Love, Joy, Peace...
መመዝገቢያ ቅጽ
ከዚህ በታች ባለው ሊንክ የመመዝገቢያ ቅጹን (PDF) አውርደው መሙላት ይችላሉ።
ስለ ማቴቴስ
ዓላማ

የመፅሐፍ ቅዱስን እውነት ትክክለኛ የስነ መለኮት መርህን በጠበቀ መልኩ በጥልቀት በማስተማር የክርስቶስን አካል የሚገነቡና የሚያንፁ እንዲሁም በአመለካከታቸዉ፤ በህይወታቸው፤ በኑሮቸዉ በህብረተሰቡ ዘንድ መልካም ተፅዕኖ ማምጣት የሚችሉ ደቀ መዝሙርትን ማፍራት ነዉ።

ራዕይ

አማኞች የክብሩ መንፅባረቅና የባህሪዉ ምሳሌ የሆነዉን ክርስቶስን ለመምሰል ራሳቸዉን በማስለመድ እየኖሩ ወደ እግዚአብሔር ፍጹም ሙላት እንዲያድጉና ለበጎ ስራ ሁሉ የተዘጋጁ አንዲሆኑ የቃሉን እውነት ማስተማር ነው።

ግብ

በቃሉና በመንፈሱ የተቃኘ የስነ መለኮት ትምህርት በመሰጠት ፦
• የእግዚአብሔርን የዘላለም ሃሳብ በሚገባ ተረድተዉ ደቀመዝሙር የሆኑና ሌሎችን ደቀመዝሙር በማድረግ የቤተክርስትያንን ተልዕኮ በዘመናቸዉ ለማከናወን ፈቃዳቸዉን የሰጡ መሪዎችን ማዘጋጀት
• ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግስት የጠራቸዉን አምላክ ማንነትና እንዲሁም ጥሪያቸዉን በግልፅ በመረዳት በዚህ የከበረ የእዉቀት ማንነት እንደሚገባ እንዲኖሩ አገልጋዮችን ማዘጋጀት
• የስማይን ስርዓት/ፈቃድ/ በምድር ላይ እንዲሰለጥን መሳሪያ የሆኑ ደቀመዝሙርትን ማፍራት
• የእግዚአብሔርን የፀጋ አሰራር በመገንዘብ የትዉልዱን አዕምሮ ለክርስቶስ መማረክ የሚችሉ አገልጋዮችን ማፍራት • ማደጋቸዉ በነገር ሁሉ የተገለፀና በበጕ ስራ ሁሉ ፍሪያማ የሆኑ መረዎችን ማፍራት
• ክርስቶስን ማዕከል ካላደረገ የሰህተት የትምህርት ንፋስ ራሳቸዉንም ሆነ ሌሎችንም መጠበቅ የሚችሉ አገልጋዮችን ማፍራት
• የክርስቶስን ዳግም መምጣት የሚናፍቁና የሚያሰቸኩሉ ቅዱሳን ሰራዊት ማስነሳት

የትምህርት ቤቱ ደንብና ምዝገባ

የትምህርት ዘመን
የዲፒሎማ ትምህርት ዘመን ርዝመት ከ24 ወር ያልበለጠ ሲሆን ርዘመቱ እንደተሳታፊዎቹ የጊዜ መመቻቸትና እንደ ትምህርቱ አሰጣጥ ሁኔታ ይወሰናል። የሰርተፊኬት ትምህርት በእንግሊዘኛ እና በአማረኛ የሚሰጥ ሲሆን የትምህርት ርዝመት ከ12 ወር ያልበለጠ ሲሆን እንደተሳታፊዎቹ የጊዜ መመቻቸትና እንደ ትምህርቱ አሰጣጥ ሁኔታ ይወሰናል።

ምልመላ
ትምህርት ቤቱ የቆመለትን ዓላማ ለማሳካት የትምህርት ዘመኑ ከመጀመሩ በፊት መመዘኛውን የሚያሟሉ ተማሪዎችን ይመለምላል።

የምልመላ መመዘኛ
አመልካቾች ሁሉ የሚከትሉትን መመዘኛዎች በአጥጋቢ ሁኔታ እንዲያሟሉ ይጠበቅባቸዋል፦ 
• በመንፈሳዊ ሕይወታቸው የተመሰከረላቸው
• ከአገልጋዮች ወይም ከሚያገለግሉበት ቤተ ክርስቲያን የድጋፍ ደብዳቤ ያላቸው • የአማርኛ ቋንቋን በሚገባ የሚረዱ በዚያም የሚሰጡ ሥራዎችን ለመሥራት መቻላቸውን ያረጋገጡ።
• ለዲፕሎማ ፕሮግራም ቢያንስ 12ኛን ክፍል በሚገባ ያጠናቀቁ። • ለሰርተፊኬት ደግሞ 10ኛ ክልፍ ያጠናቀቁ።
• አማልካቾች ከአንድ እስከ ሁለት ገጽ የሚሆን የትምህርት ደረጃቸውን ያገልግሎት ራእያቸውንና ለምን መማር እንደፈለጉ ያካተተ የህይወት ታሪካቸውን በመጻፍ ማመልከቻቸውን ለቤተ ክርስቲያን ማስገባት ይችላሉ።
• በተጨማሬም በትምህርት ቤቱ ኢሜል mathetes@ecfcks.org መላክ ይችላሉ።

ማመልከቻና ምዝገባ

መመዘኛውን የሚያሟሉ አገልጋዮች ከቤተ ክርስቲያኒቱ ድህረገጽ ወይንም በአካል ከቢሮ መመዝገቢያ ቅጽ በመውሰድና የተጠይቀውን ጥያቄ ሁሉ በማሟላት ከ $100.00 የመመዝገቢያ ክፍያ ጋር ማመልከቻቸውን ማስገባት ይችላሉ። መስፍሪያውን ሁሉ አሟልተው የምልመላውን መመዘኛ በአጥጋቢ ሁኔታ ለሚያልፉ ሁሉ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ገብተው ትምህርታቸውን ለመጀመር ተቀባይነትን እንዳገኙ የሚያበስር መልዕክት ከትምህርት ቤቱ በአድራሻቸው እንዲደርሳቸው ይደረጋል። ከዚያም በመቀጠል ለእያንዳንዱ ኮርስ $50.00 አስቀድመው በመክፍል ትምህርታቸውን መከታተል ይችላሉ። በሚመረቁበት ለምረቃ ጋውን ለመጽሄት ዝግጅትና ለመሳሰሉ ወጪዎች $100 ይከፍላሉ።

ክፍያ ዝርዝር
1. መመዝገቢያ $100 የማይመለስ
2. ጠቅላላ የትምርህት ክፍያው $600 ሲሆን በአንድ ጊዜ መክፈል እንዲሁም በሦስት ዙር አጠናቅቆ ማስገባት ይቻላል።
3. የመመረቅያ ዝግጅት ክፍያ $100
4. ጠቅላላውን የትምህርት ክፍያ ከፍሎ ነገር ግን ትምህርቱን መቀጠል ካልተቻለ በሌላ ጊዜ መማር እንዲችሉ ተቀማች ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡- ክፍያው እንደ አስፈላጊነቱ እየታየ ሊሻሻል ይችላል፡፡

የነጻ ትምህርት ዕድል
ትምህርት ቤቱ ከፍለው መማር ለማይችሉ ተማሪዎች የነጻ ትምህርት ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡

ስልቶቻችን

ትምህርት ቤቱ የተማሪዎችንና የአስተማሪዎችን የጊዜ ወይም የቦታ ውስንነትና የምንኖርበትን ሐገር የስራ ጫና ከግምት ውስጥ በማስገባት መደበኛና መደበኛ ባልሆኑ ዘዴዎች ለማስተማር የተነደፈ ሥርዓተ ትምህርት ነው። ትምህርቱ በመደበኛ የማስተማር ዘዴ ማለትም የክፍል ውስጥ የትምህርት አስጣጥ፣ በዙም፣ በቪዲዮ፣ በስልክ ኮንፍረንሶች፣ በሴሚናር፣ በተግባር ትምህርት፣ በጥናታዊ ጽሁፎችና በመሳሰሉት ዘዴዎች ይሰጣል። እነዚህም የተለያዩ ስልቶች ተማሪዎቹ በእግዚአብሄር ቃል እውቀት አድገውና በጸሎት በርትተው የነገውን ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ ደቀመዝሙር ማድረግ ወደ ሚችሉበት የመረዳት ደረጃ የክፍል ውስጥ መማርና ማስተማር እንዲሆን በታሳቢነት የሚዘጋጅ ቢሆንም የኮርሶቹ መምህራንና ተማሪዎቹ በሚስማሙበት የመማርና ማስተማር ዘዴ እንዲያካሂዱት ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ባለውአቅም ሁሉ ጥረት ያድርጋል።

ስርዓተ-ትምህርት

የተነደፈው ስርዓተ ትምህርት የቤተ ክርስቲያንዋን ወቅታዊ ፍላጎት ያገናዘበ ቢሆንም በአካባቢው ያሉ አብያተ ክርስቲያናትና ከመላው ዓለም ያሉ ተማሪዎች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ ታሳቢ ያደረገ ነው። ከሌሎች እህት አብያተ ክርስቲያናት ጋር በመተባበር አስፈላጊውን የስርዓተ ትምህርት ተግምገማና ማሻሻያ በየጊዜው ታደርጋለች። በልዩ ልዩ ምክንያት ኮርሱ ቢቋረጥ ኮርሱ በትክክለኛው መስመር እንዲቀጥልና ትምህርቱ እንዲያልቅ ቤተ ክርስቲያን በምትችለው ሁሉ ጥረት ታድርጋለች።

የሥርዓተ-ትምህርት አወቃቀር

በካንሳስ የምትገኘው የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ሕብረት ቤተክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት የስነመለኮት ስልጠና መሰረት ያደረገ ሲሆን በታቻለ መጠን መሰረታዊ የሆኑትን የስልጠና ክፍሎች ማለትም መጽሐፍ ቅዱሳዊ (Biblical)፣ ሥነ መለኮታዊ (Theological)፣ አገልግሎታዊ (Ministerial)፣ ተዋሓዳዊ (Integrated)፣ እና አጠቃላይ ወይም ልዩ ልዩ (General) ያካተተ ነው። ይህ የትምህርት ካሪኩለም ለፍላጎቶቻችን ትኩረት በመስጠት ከላይ የተጠቀሱትን ሦስት የሥነ መለኮት ትምህርት ዘርፎች ያካተተ ሲሆን ኮርሶቹም ከትምህርቱ ዘርፍ ጋር ተዛማጅነት ያለው

1. መጽሐፍ ቅዱሳዊ (Biblical) - መቅ
2. ሥነ መለኮታዊ ጥናት (Theological) -ስመጥ
3. አገልግሎታዊ (Ministerial) - አገ

አንድ ካሪኩለም በብሎክ በተርም ወይም በሴምሰተር አደረጃጀት ሊሸፈን የሚችል ሲሆን እኛ የመረጥነው የብሎክ አደረጃጀትን ስልት ነው። በከፍተኛ የትምህርት ተቁዋማት የትምህርት ጥራት መመዘኛ መሰረት አንድ ክሬዲት አወር የሚባለው በውስጡ ከ13-15 ሰዓቶች የትምህርት ጊዜያትን ያካትታል። ይህ የዲፕሎርማ ስልጠና ለከፍተኛ የትምህርት ተቋም በመጠኑ አነስተኛ ቢሆንም ስልጠናውን ተቀባይነት ባለው መልኩ ለመሸፈን አንድ ክሬዲት አወር 12 ሰአቶችን እንዲያካትት ተደርጓል። በመሆኑም ከዚህ በታች የምናያቸው ኮርሶች በዚህ ሚዛን ውስጥእንዲያልፉ ጥረት ተደርጓበታል።

በዚህ ትምህርት ቤት አገልግሎት ተኮር ስልጠና ቢሰጥም መመዘኛውን ያገናዘበ ትጋት ለማያሳዩ ተማሪዎች ችግራቸውን እንዲያስወግዱ የተቻለው እገዛና ማማከር ሁሉ ይደረጋል። ለትምህርቱ መሻሻልና መጠናከር ሲባል በአስተማሪዎች ላይ ተገቢውንና ሚዛናዊ ግምገማ በማድረግ የመማር ማስተማሩን ሒደት ለማጠናከር እንጥራለን። ችግሮች አድገው ወደ አልተፈለገ ደረጃ ይደርሳሉ ብለን ባናምንም አስቸጋሪ የሆኑና አቅምን የሚፈትኑ ችግሮች በሚከሰቱበት ጊዜ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችና የትምህርት ቤቱ ቦርድ በአንድ ላይ በመሆን ችግሩን ለመፍታት ይሞክራሉ በእግዚአብሄር እርዳትም የሚደርሱበት ውሳኔ ተፈጻሚ እንዲሆን ይደረጋል። አስተዳደር መምህራንና ድጋፍ ሰጪ አካላት ትምህርት ቤቱ በቤተ ክርስትያን አስተዳደር ሥር በመሆን ለሥራው በተመደቡ የቦርድ አባላት የሚንቀሳቀስ ነው። የቤተ ክርስቲያኒቱ የአስተዳደር ቦርድ የትምህርት ቤቱን ቦርድ በመሰየም የትምህርት ቤቱ የመማር የማስተማር ሂደት ከቤተ ክርስቲያኒቱ አውራ ራእይ ጋር በመተሳሰር የተሰየመውን ቦርድ በመጠቀም አገልግሎቱን ተፍጻሚ እንዲሆን ያደርጋል። ይህ ቦርድ የመማር ማስተማሩን ሒደት በበላይነት የሚመራና ከላይ የተጠቀሱት ራእዮችና ዓላማዎች ከግብ መድረሳቸውን በቅርበት በመከታተል ዓመታዊ ሪፕርቶችን ለቤተ ክርስቲያን አመራር ያቀርባል።

መምህራኖች

የትምህርት ቤቱ አስተዳድር ቦርድ ለእያንዳንዱ ኮርስ ብቃት ያላቸውን መምህራን በመፈለግ እና በመገምገም ቀደሚ ሥራ ይሰራል። ታሳቢ መምህራንና ድጋፍ ሰጪ አካላት ቁጥራቸው እስክ አስር የሚሆኑ በስነ-መለኮት ትምህርት በቂ እውቀት ያላቸው፣ በትምህርት ቤቶች፣ በአብያተ ክርስቲይያናትና በሲሚነሪዎች በማስተማር አገልግሎት በቂ ልምድ ያዳበሩ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት መካከልና እንዲሁም አባላት ካልሆኑ ውስጥ በቋሚነትና በእንግድነት እንዲያስተምሩ ታስቧል።መምህራኖቹ ለእያንዳንዱ የትምህርት ኮርስ የሚያስፈልገውን የትምህርት መርጃ መሳሪያና ዋቢ መጻህፍት አዘጋጅተው ለማስተማር ዝግጁ በሚሆኑበት ጊዜ ኮርሱን ይጀምራሉ።

አመራር አባላት

ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት በራሱ የቦርድና አመራር አባላት የሚመራና ተጠሪነቱ ለቤተ ክርስቲያኒቱ የሽማግሌዎች ቦርድ እንዲሆን የተቀረጸ ነው።
1. መጋቢ ሄኖክ ፀጋዬ የትምህርት ቤቱ ቦርድ ሰብሳቢ
2. መጋቢ መስፍን አብርሃም ዳሬክተርና ጸሃፊ
3. መጋቢ ሙሴ ፀጋዬ አባል
4. ወንድም እንቁ አሰፋ አባል

የተማሪ ጠባይ

እያንዳንዱ ተማሪ እንደ አጋልጋይ የመማር ማስተማሩን ሒደቱ የሚደግፍ መልካም ጠባይ ማሳየት ይኖርበታል። ከትምህርት ቤቱ ከሚመራበት ውጪ የሆነ ያልተገባ ነገር ሲያደርግ በተገኘ ተማሪ ላይ ትምህርት ቤቱ የሥነ ሥርዓት እርምጃ ይወስዳል። ተማሪዎች ከትምህርት ሰዓት ከ 15 ደቂቃ በፊት በመገናኘት የጥሞና ጊዜ እዲያደርጉ ትምህርት ቤቱ ያበረታታል። ከትምህርት ሰዓት ከተጀመረ በኋላ አርፍዶ መምጣት ግን የተከለከለ ነው። አንድ ተማሪ ትምህርቱ ከተጀመረ ከ 15 ደቂቃ በኋላ ከመጣ እንደቀሪ ይቆጠራል። አንድ ተማሪ ከሶስት ጊዜ በላይ በአንድ ትምህርት ከቀረ ኮርሱን እንዳልጨረሰ በመቁጠር ሙሉውን ኮርስ ድጋሚ እንዲወስድ ይገደዳል።

ግምገማ

በመማር እና በማስተማር ሂደት ውስጥ የተማሪዎች ተሳትፎና የአስተማሪዎች አስተዋጽኦ በየጊዜው ይገመገማል። ቀዳሚ ትኩረታችን በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ ክርስቶስ ተኮር ደቀመዛሙርትን ማፍራት ቢሆንም ተሳታፊዎች ልፋታቸውን ያገናዘበ የዋጋ አሰጣጥ እንዲተገበር ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል። የታማሪዎችን ልፋት የሚሰጠው ዋጋ ከኮርሱ አደረጃጀት ጋር በማጣጣም የትምህርት ቤቱ የማርክና ውጤት አሰጣጥ መመዘኛ በአብዛኛው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚሠራበትን አይነት መስፈርት የተከተለ ሲሆን በሚከተለው አይነት ይለካል።

የተማሪዎች ውጤት አሰጣት

Percentage Letter Grade GPA
97 – 100 A + 4.0 
93 – 96 A 3.9 
90 – 92 A- 3.7 
87 – 89 B + 3.3 
83 – 86 B 3.0 
80 – 82 B - 2.7 
77 – 79 C + 2.3 
73 – 76 C 2.0 
70 – 72 C - 1.7 
67 – 69 D + 1.3 
63 – 66 D 1.0 
60 – 62 D - 0.7 
ከ60 - በታችን F 0

ምረቃ

ትምህርታቸውን በአመርቂ ሁኔታ ያጠናቀቁ ተማሪዎች ሥራቸውን ያገናዘበ የምስክር ወረቀትና በትምህርትቻው ብልጫ ላመጡ ተማሪዎች ልዩ ሽልማቶችን ይሰጣል። ተማሪዎች በተለያየና ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ትምህርታቸውን ለማጠናቀቅ ካልቻሉ እንደ ችግራቸው ክብደትና እንዳጠናቀቁት የኮርስ መጠን ከሚቀጥሉ ምሩቃኖች (ተመራቂዎች) ጋር ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ይደረጋል። ይሁን እንጂ ይህ ውሳኔ የችግራቸው ትልቅነትና የተማሪዎቹ ትጋት ከግምት ውስጥ ገብቶ በትምህርት ቤቱ ቦርድ የሚወሰን ሲሆን ትምህርታቸውን ለሚያቋርጡ ተማሪዎች በሙሉ ከዳር እስከ ዳር ተፈጻሚነት አይኖረውም። የኮርስ መግለጫ

የአማርኛ የሰርተፊኬት ትምህርት ዝርዝሮች

የኮርስ ቁጥር የትምህርቱ ስያሜ ሰዓት
መቅ 001 የብሉይ ኪዳን ዳሰሳ 12x3= 36
መቅ 002 የአዲስ ኪዳን ዳሰሳ 12x3=24
መቅ 003 የመጽሐፍ ቅዱስ አጠናንና አፈታት ዘዴ ሄርሜኑትክስ 12x2=36
ስመጥ 004 የቤተ ክርስቲያን ዶክትሪን 1 12x3=36
አገ 005 የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ዳሰሳ 12x3=36
አገ 006 ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር 12x3=36

የእንግሊዘኛ የሰርተፊኬት ትምህርት ዝርዝሮች

Course No List of Courses Credit Hours
BS 001 Old Testament Survey 12x3= 36
BS 002 New Testament Survey 12x3=24
BS 003 How to study the Bible Hermeneutics 12x2=36
TH 004 Doctrine one 12x3=36
MN 005 Survey of Church History 12x3=36
MN 006 Introduction to Christian Ethics 12x3=36

የአማርኛ ዲፕሎማ ትምህርት ዝርዝሮች

የኮርስ ቁጥር የኮርሱ ስያሜ ሰዓት
መቅ 001 የብሉይ ኪዳን ዳሰሳ 12x3= 36
መቅ 002 የአዲስ ኪዳን ዳሰሳ 12x3=24
መቅ 003 የመጽ/ ቅዱስ አጠናን/አፈታት ዘዴ 12x2=36
ስመጥ 004 የቤተ ክርስቲያን ዶክትሪን 1 12x3=36
አገ 005 የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ዳሰሳ 12x3=36
አገ 006 ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር 12x2=24
አገ 007 የስብከት ዘዴ ትምህርት 12x2=24
አገ 008 የወንጌል ሥርጭትና ቤተ ክርስቲያን ተከላ 12x3=36
መቅ 009 የአዲስ ኪዳን መጽሃፍ ጥናት የሮሜ መጽሐፍ 12x2=24
መቅ 010 5ቱ የሙሴ መጽሃፍት 12x2=24
ስመጥ 011 ሥነ መንፈስ ቅዱስ 12x3=36
ስመጥ 012 ሥነ ክርስቶስ 12x3=36
አገ013 ፓስቶራል ካውንስሊንግ 12x3=36
አገ014 አመራር 12x3=36

ኮርሱ የሚሰጥባቸው ቀናት ጊዜያዊ ሴሌዳ
እያንዳንዱ ኮርስ የሚሰጠው የዕለቱ የክፍለ ጊዜው ርዘመት 2 ሰዓት ይሆናል። ክፍለ ጊዜው በአመዛኙ ሰኞ ምሽት እንዲካሄድ ቢታሰብም እያንዳንዱ መምህር ከተማሪዎች ጋር በመመካከር እንደ አመቺነቱ የሚወስነው ይሆናል። በዚህ ክፍል እያንዳንዱ ከላይ በሰንጠረዥ የተቀመጡት ኮርሶች ምንነትና ይዘት በዝርዝር ቀርቧል። በተጨማሪም እያንዳንዱ መምህር የሚያመጣው ሃሳብና የሚጽፈው የኮርስ መግለጫ የሚካተት ይሆናል።

መቅ 001 - የብሉይ ኪዳን ዳሰሳ

ይህ ኮርስ ብሉይ ኪዳንን ጠቅለል ባለ መልኩ ይዳስሣል። የጥንቲቱን እስራኤል ታሪካዊ(ዳራ) ስነ መሰረት በቅርቡ ይቃኛል። የብሉይ ኪዳንን መጻህፍት ለክርስቲያናዊ መልዕክት ያላቸውን ተዛማጅነት ጠቀሜታ ትኩረት በአሰሳ መልክ ያያል። ኮርሱ የብሉይ ኪዳንን ዳራ በመፈተሽ የመጽሐፍቶቹን ይዘት ዓላማ አጠቃላይ ግናዛቤ ለማሰጨበጥ ይሞክራል።

መቅ 002 - የአዲስ ኪዳን ዳሰሳ

ይህ ኮርስ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎት ላይ በማተኮር የሐዋርያትን ሚሲዮናዊ ተልዕኮ ጠቅለል ባለ ገጽታው ያቃኛል። በተጨማሪም የአዲስ ኪዳን ባህል መልክዓ-ምድር ከአዲስ ኪዳን መጽሕፍት ጋር ተዛማጅ በሆነ መልካቸው ያቃኛል። አራቱን ወንጌላት አንድነትና ልዩነት በመዳሰስ ከሌሎች የአዲስ ኪዳንና የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ጋር ያላቸውን ተዛማጅነት ይቃኛል።

መቅ 003 - የመጽሐፍ ቅዱስ አጠናንና አፈታት ዘዴ (ሄርሜኑትክስ) 

መጽሐፍ ቅዱስን በትክክል መተርጐም ለማንኛውም ክርስትና ሕይወትና አገልግሎት መሰረታዊ መሆኑ ይታወቃል። ይህ ኮርስ መጽሐፍ ቅዱስ በመጀመሪያ ሲጻፍ የተጻፈላቸው ተደራሲያን የነበሩበት ዘመን ታሪካዊ ባህልና እውቀት በመዳሰስ ቃሉ እንዴት መነበብ እንዳለበት ጠቅለል ያለ ግንዘቤ ከመስጠቱ ባሻገር መጽሐፍ ቅዱስ ሲተረጐም ቅዱሳን የወሰዷቸውን መስፈርቶች በመጠኑ ካስቃኘ በሁዋላ የወንጌል አማኞች የሚከተሉትን አተረጓጐም ስልት ያብራራል። ይህ ኮርስ ለቃላት ፍቺ አሰካክ፣ የአተረጓጐም ስልትን ያብራራል። ይህ ኮርስ ለቃላት ፍቺ አሰካክ፣ የአተረጓጐም መስመርና ለመሳሰሉት በተዛማጅ መልኩ በቂ ሽፋን ይሰጣል። በዚህ ኮርስ መጽሐፍ ቅዱስን ከአፈ ታሪክ፣ ከሌሎች ጽሁፎች ከህልሞችና ከመሳሰሉት በተለየ ሁኔታ በቀጥታ የሚተረጐምበትን አፈታት ያስቃኛል።

ስመጥ 004 - የቤተ ክርስቲያን ዶክትሪን

ይህ ኮርስ መሠረታዊ የክርስትና አስተምህሮ በቅርበት ይቃኛል። አውራ የሆኑ የመሰረተ ክርስትና ርዕሰ ጉዳዮችን በአሰሳ መልክ ለመሸፈን ይሞክራል። ከእነዚህም ርዕሰ ጉዳዮች እግዚአብሄር አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ፣ መጽሐፍ ቅዱስ፣ መላዕክት፣ ሰው፣ ደህንነት ቤተክርስቲያንና ዘመነ ፍጻሜ ይዳሰሳሉ። እነዚህ ርዕሰ ጉዳዮች ከዘመናችን ቤተ ክርስቲያን ጋር ባላቸው ተዛማጅ ገጽታ ዙሪያ ጠቅለል ያለ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ይሞክራል።

አገ 005 - የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ዳሰሳ

ይህ ትምህርት ከበዓለ ሃምሳ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን የቤተ ክርስቲያን እድገት ይዳስሳል። እግዚአብሔር በታሪክ ውስጥ የተጠቀመባቸውን ቁልፍ ሰዎች እና ክንውኖች እና እንዲሁም ቤተ ክርስቲያን የፈጸመችውን ተጽእኖዎች ይሸፍናል። ዛሬም ቤተ ክርስቲያን ራሷን እና አምላኳን በደንብ እንድታውቅ እንዲሁም እጅግ ተለዋዋጭ በሆነ ዓለም ውስጥ ስታልፍ የእግዚአብሔር ልጅ መገለጥ ነው።

አገ 006 ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ትምህርት (ክርስቲያናዊ ኤትክስ)

ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ትምህርት መጽሐፍ ቅዱስ መሠረት በማድረግ የኢየሱስ ክርስቶስን ትዕዛዝ፣ በብሉይ ኪዳን ነቢያት እና በአዲስ ኪዳን ሐዋርያት ትምህርት ላይ የተመሰረተ የትክክለኛና የስህተት መመዘኛዎች ማሳውቅ ነው።

አገ 007 የስብከት ዘዴ (ሆሞለቲክስ)

ይህ ኮርስ ስለ ስብከት አይነቶችና ዘዴዎች ክርስትናዊ ትምህርት በዘመናችን ምን መምሰል እንዳለበት ይቃኛል። ለአንድ ክርስቲያናዊ ማኅበረሰብ ጠቃሚ የሆነ ስርዓተ ትምህርት ሊያካትታቸው የሚገቡ አውራ ጉዳዮችን በቅርበት ይቃኛል። በዘመናችን የክርስቲያን ትምህርት ውጤታም ስለሚሆንበት ሁኔታና ወንጌልን ስለማስተማር ዘዴዎች ይቃኛል።

አገ 008 - የወንጌል ሥርጭትና ቤተ ክርስቲያን ተከላ

ይህ ኮርስ ወንጌል ስርጭትና የቤተ ክርስቲያን ተከላ መሠረታዊ አስተምሮዎችን ይዳስሳል። በተጨማሪም ስለአጥቢያና አለም አቀፋዊቱ ቤተ ክርስቲያን አንድነትና ልዩነት የቤተ ክርስቲያን ተከላ ዓላማና መርሆችን ያሳያል። የቤተ ክርስቲያን አስተዳደርንና የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አመሠራረትን ያስተምራል። በዘመናችን ያሉትን አብያተ ክርስቲያናት ድካምና ጠንካራ ጐኖች አውጥቶ ይወያያል። የወንጌልን ስርጭት ዘዴዎች በተለያዩ ተሞክሮዎች ይቃኛል። በሐገራችን ያለውን የቤተ ክርስቲያን ተከላ አካሔድ ከሌሎችም ምዕራባውያን ጋር በማነጻጸር ይወያያል።

መቅ 009 - የሮሜ መጽሐፍ

የዝርዝር መጽሐፍ ቅዱስ አጠናን ዘዴን በመጠቀም ሐዋርያው ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች የጻፈውን መል ዕክት በዝርዝር ማጥናት ሲሆን በዚህ መጽሀፍ የተተኮረባቸውን ኃጢአት፣ ጽድቅ፣ ሕግ፣ ቅድስና፣ መመረጥ፣ . . . ወዘተ እንዲሁም

መቅ 010 - አምስቱ የሙሴ መጽሃፍት (ፔንታቱክ)

የመጽሃፍ ቅዱስ አጠናን ዘዴን በመጠቀም በጥልቅት እነዚህ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ በማጥናት ጸሐፊው ሙሴ በጊዜው የእግዚአብሄርን ፈቃድ የተቀበለበትን፣ ፈቃዱን የታዘዘበትን፣ የፈጸመበትን በማጥናት ለዚህ ዘመን ደግሞ ያለውን መልዕክት በዝርዝር ማጥናትና መረዳት ሲሆን በዚህ መጽሀፍ የተተኮረባቸውን ጭብጥ ሃሳብ ለማሳወቅ ይጥራል።

ስመጥ 011 - ሥነ መንፈስ ቅዱስ (ኒዮማቶሎጂ)

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ማንነትና ሥራ የሚያስተምራቸው እውነቶች በዚህ ኮርስ በቅርበት ይቃኛሉ። መንፈስ ቅዱስ ለቤተ ክርስቲያን ህይወት ሊሰጠው ስለሚገባ ትኩረት ተሳታፊዎች ተገቢውን ግንዛቤ እንዲጨብጡ ተግባራዊ ርምጃ ይወስዳል። በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችና ፍሬዎች መካከል ሚዛን የጠበቀ እይታ እንዲኖር ኮርሱ የበኩሉን እገዛ ያደርጋል። የመንፈሳዊ ስጦታዎች አጠቃቀም መጽሀፍ ቅዱሳዊ ቅርጽ በሚይዝባቸው ተግባራዊ ሁኔታዎች ላይ ተገቢ ትኩረት እንዲደረግና ግራ የማቴቴስ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ሕብረት ቤተ ክርስቲያን በካንሳስ መጋባት ከዘመናችን አብያተ ክርስቲያን እንዲወገድ ኮርሱ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ተሳታፊዎቹን ያበረታታል። የጠራ የነጠረ የመንፈስ ቅዱስ አመራር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለሚዘወተርበት ሁኔታ ተሳታፊዎቹ የበኩላቸውን እንዲያዋጡ የበኩሉን እገዛ ለማድረግ ይጥራል።

012 ሥነ ክርስቶስ (ክርስቶሎጂ)

የዚህ ትምህርት ዋና ግብ የክርስቶስን ማንነት ትምህርትና ሥራ በጥልቀት መዳሰስ ነው። ትምህርቱ በዝርዝር የሚሸፍናቸው፦ የኢየሱስ ክርስቶስ ቅድመ - ህልውና። የኢየሱስ ክርስቶስ መሲሕ ነኝ የወንጌላት ዋና ጭብት ስለመሆኑ። የክርስቶስ አምላክነት፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ሰብአዊነት ወዘተ።

አገ 013 የምክር አገልግሎት (ፓስቶራል ካውንስሊንግ)

ይህ የምክር አገልግሎት ትምህርት በመጽሃፍ ቅዱስ እውነት ላይ የተመሰረተ ተግባራዊ እውቀት እና ክህሎቶች በማስጨበት ተማሪዎች የሌሎች ሰዎች ህይወት ጉዳዮች ውስጥ እንዲሰሩ ለመርዳት የሚያዘጋጃቸውን ዘዴ ማሳወቅ ነው።

አገ 014 - አመራር (ሊደርሽፕ)

በዓለማችንና በቤተ ክርስቲያን የሚነሱ ውዝግቦችን ሙሉ በሙሉ ከአመራር ጋር የተያያዘ ገጽታ እንዳላቸው ይታመናል። ይህ ኮርስ ክርስቲያናዊ አመራር ምንነትን፣ ከሌሎች አመራሮች ጋር የሚመሳሰሉበትንና የሚለያዩበትን ጐኖች ይዳስሳል። የተሻለ የሚለውን የአመራር ስልት በቅርበት ቃኝቶ ለቤተ ክርስቲያን ግንባታ እንዴት እንደምንጠቀምበት መርምሮ ተግባራዊ አደራረጉን ያሳያል።ይህ ኮርስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስለሚኖሩት የአገልግሎት ዘርፎች አገልጋዮችን በጸጋቸው ለወንጌል ሥራ ስለማሰማራት የቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና አወቃቀር ዘዴዎች ያካትታል። በተጨማሪም ስለጌታ እራት ምንነትና አሰጣጥ ስለሰርግ እና ስለቀብር ስነስርዓቶች ስለመሳሰሉት ሁሉ